top-news-1350×250-leaderboard-1

አሜሪካ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ተኩስ አቁም እንዲደረግ በድጋሚ ጥሪ አደረገች

የአሜሪካ መንግሥት፣ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ በመቀጠል ላይ ያለው ግጭት እንዲቆም ጥሪውን በድጋሚ አሰምቷል።

የኤም 23 አማፂያን በርካታ ቦታዎችን በመቆጣጠር ላይ ባሉበት በዚህ ወቅት፣ የአሜሪካንን መንግሥት ጥሪ በድጋሚ ያሰሙት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ታሚ ብሩስ፣ የውጪ ጉዳይ ምኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ ከዚህ በፊት በጉዳዩ ላይ ያሳዩትን አቋም በድጋሚ አንጸባርቀዋል።

ሩቢዮ ከሩዋንዳው ፕሬዝደንት ፖል ካጋሜ እና ከኮንጎው ፕሬዝደንት ፊሊክስ ቸሰደኪ ጋራ መነጋገራቸውን ያወሱት ቃል አቀባዩ፣ ግጭቱ በአስቸኳይ እንዲቆምና ለተከሰተው የሰብአዊ መብት ጥሰት ተጠያቂነት እንዲኖር ማስገንዘባቸውን ተናግረዋል።

ለኮንጎ ሕዝብ እና ለኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ሉአላዊነት ያላቸውን ድጋፍ የውጪ ጉዳይ ምኒስትሩ ማስታወቃቸውንም ቃል አቀባዩ አመልክተዋል።

አሜሪካ በአንጎላው ፕሬዝደንት ሉዋንዳ ላይ ባለፈው ዓመት የተጀመረውንና የተኩስ ማቆም ስምምምነት እንዲፈረም ያስቻለውን ሂደት እንደምትደግፍም ቃል አቀባዩ አስታውቀዋል።

አሜሪካ በዲፕሎማሲ በኩል ግኑኙነቷን እንደምትቀጥልም ተናግረዋል። የአፍሪካ ኅብረት፣ የተመድ የጸጥታው ም/ቤት እንዲሁም አሜሪካ በኮንጎ የሚታየውን ሁከት አውግዘዋል።

ተመድና አሜሪካ፣ ሩዋንዳ የኤም 23 አማፂያንን እንደምትደግፍና ሠራዊቷንም በምስራቅ ኮንጎ ማሰማራቷን ሲገልጹ፣ ሩዋንዳ ታስተባብላለች፡፡

በቅርቡ በአዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት ጉባኤ ላይ አሜሪካ ለ90 ቀናት የውጪ ርዳታ ማቋረጧ በሰብአዊ፣ ደኅንነትና ጤና መስኮች ሊደርስ የሚችለው ጉዳት እንደሚያሳስባቸው የአህጉሪቱ መሪዎች አሜሪካ አስታውቀዋል።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ታሚ ብሩስ በበኩላቸው፣ የማቋረጡ ውሳኔ መንግሥት ለውጪ ርዳታዎች የሚውለውን ገንዘብ እንደገና ለመመልከት እና የሚሠራና የማይሠራውን ለመለየት ጊዜና ዕድል እንዲሰጠው ይረዳል ሲሉ ተከላክለዋል።

ውሳኔው አሜሪካ ከዚህ በኋላ ርዳታ እንደማትሰጥ የሚያለክት ሳይኾን፣ ውጤታማ የሆነውን የርዳታ ዐይነት ለመለየት የሚጠቅም ነውም ብለዋል።

ሰዎች ርዳታ እንዳይቋረጥባቸው ለውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚያመለክቱበት ሂደትም እንዳለ ጠቁመዋል።

Crédito: Link de origem

Leave A Reply

Your email address will not be published.