ሶማሊያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የእስላማዊ መንግሥት ቡድን ታጣቂዎች፣ ከፑንትላንድ ጦር ጋር ለሁለት ወራት ካደረጉት ተከታታይ ውጊያ በኋላ፣ እንዲያፈገፍጉ ማድረጉን የክልሉ ባለሥልጣናት ተናግረዋል።
ባለፈው ሳምንት የፑንትላንድ ጦር በቡክ ካሌድ የቡድኑን አሚር አብዱልቃድር ሙሚን ዋና መሥሪያ ቤት በቁጥጥር ስር አውሏል።
የአካባቢው ባለሥልጣናት በኩራ መንደር አቅራቢያ በተካሄደ ውጊያ 15 ወታደሮች መሞታቸውን ገልጸው፣ አይ ኤስ የሞቱበትን 57 ተዋጊዎች ጥሎ መሸሹን አስታውቀዋል፡፡
ከሳምንት በኋላ አይ ኤስ ወይም አይሲስ ተብሎ የሚጠራው የሽብር ቡድን ተጨማሪ አጥፍቶ ጠፊዎችን እና አዲስ ተዋጊዎችን ይዞ በሸለቆው አካባቢ መልሶ ማጥቃት ጀምሮ እንደነበር ባለሥልጣናቱ ገልጸዋል፡፡
የፑንትላንድ ጦር የሽብር ቡድኑን ሦስት የጦር ሰፈሮችን ከመቆጣጠሩ በፊት፣ በውጊያው ወደ 100 የሚጠጉ ሰዎች የሞቱ ሲሆን 28 ወታደሮችን እና ከ70 በላይ ታጣቂዎችን መገደላቸው ተዘግቧል።
እንደ ባለሥልጣናቱ ገለጻ የፑንትላንድ ወታደሮች ከቱርማሳሌ እስከ ዳሳን ያለውን 40 ኪሎ ሜትር ስልታዊ ኮሪደር በማጽዳት ዋሻዎችን እና ትናንሽ መንደሮችን ተቆጣጥረዋል።
የፑንትላንድ ኃይሎች ዋሻዎችንና ትናንሽ መንደሮችን አከታትለው ሲቆጣጠሩ የአይኤስ ተዋጊዎችን ስትራቴጂያዊ ይዞታቸው ከኾኑት የቶጎ ውጫሌ ሸለቆ፣ ከቱርማሳሌ እና ከደሃሳን በ40 ኪሎ ሜትሮች በላይ እንዲያፈገፍጉ ማድረጋቸውን ባለሥልጣናቱ ገለጸዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር ስለ አይ ኤስ ማፈግፈግ ሲጠየቅ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆነም። ይኹን እንጂ ግን ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ አንድ የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ባለሥልጣን በሂደት ላይ ስላለው ኦፕሬሽን ሲናገሩ “ዋሽንግተን ተጨማሪ ርዳታ ለመስጠት መዘጋጀቷን ጠቁመዋል።
“በአፍሪካ ቀንድ አሸባሪ ድርጅቶችን ለመበተን፣ ለማመናመን እና ለማሸነፍ በምናደርገው የጋራ ጥረት አጋሮቻችንን ለመደገፍ ቁርጠኛ ነን” ሲሉ ባለሥልጣኑ ለቪኦኤ ተናግረዋል።
የፑንትላንድ ክልል መሪ ሳይድ አብዱላሂ ዴኒ “ አሸባሪዎች እንቅስቃሴያቸው እና መሠረቶቻቸው በሙሉ እስኪወገዱ ድረስ” የሽብር ቡድኑን አድነን ለማጥፋት ዝግጁ ነን” ሲሉ ዝተዋል።
የሶማሊያ ባለሥልጣናት ለአሜሪካ ባለሥልጣናት ሲናገሩ የአይ ኤስ ተዋጊዎች ይዞታቸው ላይ ከመቆየት ይልቅ በሦስት ቡድኖች ተከፋፍለው በተለያዩ አቅጣጫዎች ሸሽተዋል” ብለዋል።
የሶማሊያ የጸጥታ ባለሞያዎች ግን ግፊቱ ተጠናክሮ ካልቀጠለ በስተቀር ቡድኑ እንደገና በመሰባሰብ የሽምቅ ውጊያ ሊጀምር እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
Crédito: Link de origem