top-news-1350×250-leaderboard-1

እስራኤል በጋዛ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ለማድረግ የአሜሪካን ዕቅድ ስትደግፍ ሀማስ ተቃውሟል

የእስራኤል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፤ በእስራኤል እና ሀማስ መካከል የተደረሰው ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ሊያበቃ የሰዓታት ጊዜ በቀሩት ወቅት፤ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልዑክ የሆኑት ስቲቭ ዊትኮፍ፤ በረመዳን እና በፋሲካ የጾም ወቅት በጋዛ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ያቀረቡትን ሀሳብ ሀገራቸው መቀበሏን እሁድ ማለዳ አስታውቋል።

ዊትኮፍ ባቀረቡት ዕቅድ መሰረትም በመጀመሪያው ቀን በጋዛ በህይወትም ያሉት እና ከሞቱትም ታጋቾች ግማሾቹ እንደሚለቀቁ የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጽህፈት ቤት የገለጸ ሲሆን፥ ቀሪዎቹ ታጋቾችም ዘላቂ የሆነ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ከተደረሰ በኋላ እንደሚለቀቁ ገልጿል።

ዊትኮፍ በቋሚ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመነጋገር ተጨማሪ ጊዜ እንደሚያስፈልግ በመረዳታቸው፤ አሁን ያለውን የተኩስ አቁም ለማራዘም ሀሳብ አቅርበዋል ሲል የኔታኒያሁ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

በዩናይትድ ስቴትስ አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው የሐማስ ቡድን ቃል አቀባይ ሀዜም ቃሴም ከቅዳሜ ዕለት ቀደም ብሎ ቡድኑ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት የመጀመሪያ ምዕራፍ መራዘሙን ውድቅ ማድረጉን ቢገልጹም የዊትኮፍ እቅድን በግልፅ አልጠቀሱም።

እስራኤል በዊትኮፍ እቅድ ላይ ሀማስ ከተስማማ ወዲያውኑ ድርድር ታካሂዳለች ሲል የኔታኒያሁ ቢሮ አስታውቋል።

“በስምምነቱ መሰረት እስራኤል ከ42ኛው ቀን በኋላ ድርድሩ ውጤታማ እንዳልሆነ ከተሰማት ወደ ጦርነት መመለስ ትችላለች” በማለት የኔታኒያሁ ጽህፈት ቤት ሀማስ ስምምነቱን ጥሷል ሲል ከሷል።

ሁለቱም ወገኖች አንዱ ሌላኛውን ስምምነቱን ጥሷል በሚል ሲከሱ ቆይተዋል።

ስለድርድሩ የሚያውቁ ሁለት የፍልስጤም ባለሥልጣናት ለሮይተርስ እንደተናገሩት እስራኤል ወደ ሁለተኛው የስምምነት ምዕራፍ ለመግባትም ሆነ በዚህ ጉዳይ ላይ ድርድር ለመጀመር ፈቃደኛ አልሆነችም ብለዋል።

በምትኩ፣ እስራኤል ሳምንታቶቹን በማራዘም ለተራዘመው ለእያንዳንዱ ሳምንት በርካታ ታጋቾችን እና አካላት እንዲለቀቁላት ጠይቃለች።

ቅዳሜ ዕለት የሀማስ ታጠቂ ክንፍ የእስራኤል ታጋቾች አሁንም በጋዛ በእስር ላይ እንደሚገኙ የሚያሳይ ቪዲዮ የለጠፈ ሲሆን፤ የተቀሩት ታጋቾች ሊፈቱ የሚችሉት በጎርጎርሳውያኑ ጥር 19 የተጀመረው የተኩስ አቁም ስምምነት ሲጠናቀቅ ብቻ መሆኑን አፅንዖት ሰጥቷል።

የተኩስ አቁም ንግግሮች በቅርቡ በካይሮ ቢደረጉም ስምምነት ላይ ሳይደረስ ተጠናቀዋል።

በተያያዘ ዜና ዛሬ እሁድ እስራኤል ሀማስ በቋፍ ላይ ያለውን የተኩስ አቁም የማይቀበል ከሆነ ወደ ጋዛ ሰርጥ የሚገቡ ምርቶችና ሸቀጦችን እንደምትገድብ እና “ተጨማሪ መዘዞች” እንደሚከተሉ አስታውቃለች።

ሀማስ እስራኤል ጫፍ ላይ ያለውን የተኩስ አቁም ስምምነት ለማደናቀፍ እየሞከረች ነው በማለት የከሰሰ ሲሆን፤ ዕርዳታውን ለማቆም የወሰነችው ውሳኔም “ርካሽ ዘረፋ፣ የጦር ወንጀል እና ግልጽ ጥቃት” ነው ብሏል።

Crédito: Link de origem

Leave A Reply

Your email address will not be published.