top-news-1350×250-leaderboard-1

ቻይና “ከታይዋን ጋር የምፈጽመው ‘ዳግም ውህደት’ ሰላማዊ እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት አደርጋለሁ” አለች

ቻይና “ከታይዋን ጋራ የምፈጽመው ‘ዳግም ውህደት’ ሰላማዊ እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት አደርጋለሁ” አለች። ከታይዋን ጋራ የምታደርገውን የዳግም ውህደት ‘ሰላማዊነት’ ለማረጋገጥ ‘ከፍተኛ ጥረት እንደምታደርግ፤ ነገር ግን የአገር ግዛት አንድነቷን ለማስጠበቅ ‘አስፈላጊ’ ያለቻቸውን ርምጃዎች ሁሉ እንደምትወስድ፣ የቻይና የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ዛሬ አስታወቀ።

ታይፔ ተቃውሞ ብታቀርብም፤ ቻይና ግን በዲሞክራሲያዊ መንገድ የምትተዳደረውን ታይዋንን “ግዛቴ ነች’ ትላለች። የታይዋኑ ፕሬዝደንት ላይ ቺንግ-ዶ በበኩላቸው ‘የአገሩን መጭ እጣ መወሰን የሚችለው የታይዋን ሕዝብ ብቻ ነው’ ሲሉ መልሰዋል።

በተያያዘ ሌላ ዜና፣ የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ባለፈው ሳምንት ከተካሄደው የቤጅንጉ ዓመታዊ የፓርላማ ጉባኤ ትይዩ ለጋዜጠኞች በሰጡት አስተያየት፤ ታይዋን መቼም ቢሆን “ሀገር” አትሆንም፤ “የታይዋንን ነፃ አገር የመኾን ፍላጎት” መደገፍም በቻይና የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት የሚቆጠር ነው’ ሲሉ ተደምጠዋል። የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ታይዋንን አስመክቶ ስለ ሰጡት ስለዚህ አስተያየታቸው የተጠየቁት የውጭ ጉዳይ ሚንስቴሩ ቃል አቀባይ ማኦ ኒንግ በበኩላቸው፤ ቻይና “በሰላማዊ መንገድ የሚፈጠር ዳግም ውህደት እውን ለማድረግ ‘የተቻላትን ሁሉ ለማድረግ’ ፍቃደኛ ነች” ብለዋል።

ቃል አቀባይዋ አያይዘውም፡ አገራቸው “በተመሳሳይ ብሔራዊ ሉዓላዊነቷን እና የግዛት አንድነቷን ለማስከበር ሁሉንም አስፈላጊ ርምጃዎች ትወስዳለች። የታይዋንን ነፃ አገር መሆን እና የውጭ ጣልቃገብነትን በፅኑ ትቃወማለች” ብለዋል።

ቤጂንግ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በደሴቲቱ አገር ላይ የምታደርገውን ወታደራዊ ጫና ማሳደጓ ይታወቃል። ከዚህም ውስጥ የተለያዩ ወታደራዊ ልምምዶች ሲገኙበት፤ ታይዋንን በቁጥጥር ስር ለማዋል የኃይል አማራጭን ከግምት ያስገባ ርምጃን እውንነት የሚያመላክት መሆኑ ተዘግቧል። እንደ ሃገር መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ባይኖራት እና ከጃፓንና ደቡብ ኮሪያ ያላትን የመሰለ ልዩ የመከላከያ ውል በመሃከላቸው ባይኖርም፤ ዩናይትድ ስቴትስ ዋነኛዋ የታይዋን የጦር መሳሪያ አቅራቢ መሆኗ ይታወቃል።

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይዋ ማኦ ለጋዜጠኞች በሰጡት አስተያየት አክለውም፤ ‘ዩናይትድ ስቴትስ ከታይዋን ጋራ የምታደርገውን የጦር መሳሪያ ሽያጭ ማቆም እና ከደሴቲቱ ጋራ ያላትን ወታደራዊ ግንኙነትም ማቆም አለባት ብለዋል። “የታይዋን ጉዳይ የቻይና መሰረታዊ ጥቅም እና በቻይና እና በዩናይትድ ስቴትስ ግንኙነት የመጀመሪያው የማይታለፍ ቀይ መስመር ነው” ሲሉም አስጠንቅቀዋል።

Crédito: Link de origem

Leave A Reply

Your email address will not be published.