top-news-1350×250-leaderboard-1

በብዙ አገሮች የሽብር ጥቃቶች እየበረከቱ በመጡበት አፍሪካ አስከፊ ጥቃቶችን ማስተናገዷ ተዘገበ

ባለፈው ዓመት በዓለም እጅግ አውዳሚ መሆኑ የተነገረለት የአሸባሪዎች ጥቃት በአፍሪካ ሲፈፀም፤ የዓለም የምጣኔ ሃብት እና የሰላም ተቋም ይፋ ያደረገው የ2025 የዓለም አቀፍ የሽብር ጥቃቶች ጠቋሚ ሪፖርት እንዳመለከተው፤ በአጠቃላይ ከሽብር ጋር ከተዛመዱ ግድያዎች ከገሚስ በላይ የሚሆኑት የተፈጸሙት የዓለም አቀፍ የሽብር ጥቃቶች መናሃሪያ ሆኖ በቆየው የሳሕል ክልል ነው።

በሁለት ሀገራት የደረሱትን 3 አደገኛ የሽብር ጥቃቶች ጨምሮ በዓለም ዙሪያ ከተዘገቡት 20 ያህል እጅግ የከፉ ጥቃቶች ውስጥም 17ቱ የተፈጸሙት በአፍሪካ ነው። ባለፈው ዓመት በሰኔ፣ በሀምሌ እና በነሀሴ ወር በኒጀር እና ቡርኪና ፋሶ የተፈጸሙት ጥቃቶች ለ607 ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክኒያት መሆናቸውን አክሎ ዋና መሥሪያ ቤቱን በአውስትራሊያ ያደረገው ይሄው የጥናት ቡድን አረጋግጧል።

በዚሁ ዓመት በሳህል ክልል ከግጭቶች ጋር ተያይዘው የደረሱ ሞቶች ቁጥር ከ25,000 በላይ ሰዎች የጠፋባቸው ድንገቶች ዓመታዊው ጥናታዊ ሪፖርት ይፋ መደረግ ከጀመረ ወዲህ ከተዘገቡት ሁሉ እጅግ ግዙፍ መሆኑ እና ከእነዚህም ውስጥ 3,885 ያህሉ በአሸባሪዎች የተፈጸሙ መሆናቸው ተመልክቷል። በመሰል የአሸባሪዎች ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸው ሃገራት ቀዳሚዋ ቡርኪና ፋሶ ስትሆን፤ ብርቱ ጉዳት ከደረሰባቸው ጥቂት የአፍሪካ ሀገሮች ማሊ፣ ኒጀር፣ ናይጄሪያ፣ ሶማሊያ እና ካሜሩን እንደሚገኙባቸው ታውቋል።

ቡርኪና ፋሶ በዘገባዎች እንደተገለጸው ክፉኛ የተጎዳች ሀገር ብትሆንም፤ አጠቃላይ የጥቃት እና የሟቾች መጠን የሚያመለክቱ አሃዞች በጠቅላላው በ21 በመቶ እና በ57 ቀንሰዋል። ያም ሆኖ ቡርኪና አሁንም በአለም አቀፍ ደረጃ በአሸባሪዎች በሚደርሱ ጥቃቶች የከፋ አደጋ ከሚደርስባቸው አምስተኛዋ አገር ነች።

በዓመቱ ውስጥ ቢያንስ አንድ የሽብር ጥቃት የደረሰባቸው ሀገራት ቁጥር ከ58 ወደ 66 ከፍ ማለቱንም ሪፖርት አክሎ አስፍሯል። ከዚህም ውስጥ ከእስላማዊው ጽንፈኛ ቡድን አይሲስ ጋር ቁርኝት ያላቸው ቡድኖች በዓለም ዙሪያ በ22 የተለያዩ አገሮች ውስጥ ባደረሷቸው የሽብር ጥቃቶች 1, 805 ሰዎች ተገድለዋል። በሌላ በኩል እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2024 በሽብርተኞች የተፈጸሙ ጥቃቶች ቁጥር ወደ 7,555 ዝቅ ማለቱ ሲዘገብ፣ ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ13 በመቶ ያነሰ መሆኑ ታውቋል።

Crédito: Link de origem

Leave A Reply

Your email address will not be published.